top of page

ጥንታዊው የሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሽመልስ አብዲሳ በተላከ ህገወጥ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት። (ኢትዮ 360-ሚያዚያ 11/2015)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊው የሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሽመልስ አብዲሳ በተላከ ህገወጥ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስበት መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። በተደጋጋሚ አበካባቢው ሲመላለሱ መታየታቸው የሚገለጸው ይሄው የወንጀለኛው ቡድን ስብስቦች ትላንት ምሽት ቤተክርስቲያኑን ሰብረው ገብተው ጉዳት ማድረሳቸውን ይናገራሉ። ከቤተክርስቲያኑ አልፈው ሰሞኑን በተደጋጋሚ የእምነቱ ተከታይ በሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ዛቻ ሲሰነዝር የቆየው ይሄው ቡድን በነሱ ላይም ጥቃት መሰንዘሩን ነው ምንጮቹ ያመለከቱት። በተለይ ሽመልስ አብዲስ የሚመራውን በወንጀለኞች የተሞላው ክልል ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ምዕመናን ብሎም ካህናት ላይ የሚደርሰው ግፍ አሁም ተጠናክሮ መቀጠሉን ያነሳሉ።


የዚህ አካል የሆነው ወንጀል ደግሞ ትላንት ምሽትከናዝሬት 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውንና በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፖትርያሪክ የተመሠረተው ቤተክርስቲያን ላይ ተፈጽሟል ይላሉ። በቀላሉ የቤተክርስቲያኑ በር መስበር ያልቻለውና ቁጥሩ ከ50 በላይ የሚሆነው የወንጀለኞች ስብስብ በሩን ሰብሮ መግባቱንና በውስጥ የነበሩ የቤተክርስቲያኗን ንብረቶች ማውደሙን አመልክተዋል። ግንቦት ላይ ቅዱስ ሲኖዶሱን ለመቆጣጠ እቅዱን ሰርቶ የጨረሰው የአብይ አህመድና የነሽመልስ አብዲሳ ስብስብ አስቀድሞ አብያተ ክርስቲያናትን ማውደምና ምእመናኑን እንዲሁም ካህናቱን ማሰቃየቱን ቀጥሏል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።

Recent Posts

See All

ነሃሴ 18/2015 በሰሜን ሸዋ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ /መኮይ/ ገና በጠዋቱ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። ገና ሳይነጋ ንጹሃንን ሊፈጅ ወደ በአንጾኪያ...

ነሐሴ 18/2015 የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ገለጹ።

በደቡብ ክልል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ክልል ውስጥ ያሉው የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ። አዲስ ተቋቋመ በተባለውና ከፍተኛ ቁጥር...

bottom of page