የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶችን በፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ስር ለማድረግ የማሳመኛ ዶክመንት ተዘጋጅቶ መላኩን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አጋለጡ።
ይሄንን ዶክመንት ያጠናው ደግሞ በአብይ አህመድ የተቋቋመውና ተጠሪነቱም ለእሱ የሆነው የገዳዩና አፋኙ የእስኳድ ቡድን መሆኑንም ተናግረዋል።
ይሄ ቡድን የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶችን ከአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ኮሚሽን ጥበቃ ስር አንስቶ በፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ስር ለማድረግ የማሳመኛ ዶክመንት አዘጋጅቷል ይላሉ።
ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀም ይሄንን ዶክመንት በቀጥታ የቡድኑ የፖለቲካ ክንፍ አስፈፃሚ ለሆነው ለሽመልስ አብዲሳ መስጠቱን የውስጥ ምንጮቹ ይናገራሉ።
ይሄ ቡድን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበት ዋነኛ አላማም አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ በሁሉም የአማራ አካባቢዎች በመንግስት የሚታፈኑ ንቁ አማሮችን በከፍተኛ ሚስጥር ወደተዘጋጀው እስር ቤት በመውሰድ ቶርች ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ነው ብለዋል።
ቡድኑ እስካሁን ኮሚሽነር ወንድሙ ጫቃ በሚባል የአብይ አህመድ አምላኪ በሆነ ግለሰብ የሚመሩ ሁለት ሚስጥራዊ እስር ቤቶችን በማቋቋም ጥቅም ላይ ማዋሉንም ሳይጠቁሙ አላልፉም።
እነዚህ ሚስጥራዊ ማፈኛ ስፍራዎች አንደኛው በመሀል አዲስ አበባ ኢሊሌ ሆቴል ምድር ቤት ውስጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ገላን በሚወስደው ሀይዌይ መንገድ ስር አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ የሚገኝ እና ገና ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለዚህ አላማ ሲባል በይፋ ያልተመረቀ ማረሚያ ቤት መሆኑንም አጋልጠዋል።
እስካሁን የሚታፈኑ የአማራ ተወላጆችም ሆኑ ሌሎቹ በነዚህ ማፈኛ ቤቶች እየተሰቃዩ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ማሰር፣መግደልና ማሳደድ ያልበቃው የአፓርታይዱ መሪ አብይ አህመድ አሁን ደግሞ የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ባደራጀው ቡድን በኩል ጥናቱን አድርጎ ጨርሷል ብለዋል።
በቀጣይም የአማራ ክልልን ማረሚያቤቶች በፌደራል ፖሊስ ስም በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ንቁ ናቸው የተባሉ የአማራ ተወላጆችን ወደዚህ ሚስጥራዊ ማሰቃያ እስር ቤት በማጋዝ ቶርች በማድረግ እና በማሳቀቅ ከትግል መስመር ማስወጣት የሚል ስውር እቅዳቸው መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አረጋግጠዋል።