top of page

ግንቦት 10/2015 በአፋር ክልል በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለከፋ ረሃብ ተዳርገዋል።


በአፋር ክልል በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውንና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን የሚረዳቸው አካል በመጥፋቱ ለከፋ ረሃብ መዳረጋቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



በተለይ ራሱንና ቤተሰቡን በሃብት እያደላደለ ያለው የአወል አርባ አስተዳደር በረሃብ እየተገረፉ ያሉ ዜጎችን መመልከት አለመቻሉ ችግሩን አክፍቶታል ይላሉ።



ሙሉ በሙሉ የአፋር ህዝብ በሚባል ደረጃ አሁን ላይ ለከፋ ችግር ተዳርጓል ሲሉ ምንጮቹ ይናገራሉ።


ህዝቡ በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሆኖ ግን የወል አርባ ለህጻን ልጁ ስም ሳይቀር ትልልቅ ህንጻዎችን እየገነባ መሆኑን ነው ጨመረው ያመለከቱት።



ተመልካች ያጣው የአፋር ህዝብ አካባቢውን ለቆ ለመሰደድ በሚያደርገው ሙከራም ህይወቱን እያጣ መሆኑን ይናገራሉ።



ለዚህ ደግሞ ሰሞኑን በአፋር ኤሊዳአር ከተማ ቁጥራቸው ወደ 300 የሚሆኑ የአፋር ወጣቶችን የጫነና ከሃገር ሊወጣ የተዘጋጀ ተሽከርካሪ ተገልብጦ በቁጥር በትክክል ያልታወቁ በርካታ ወጣቶች ህይወታቸው ማለፉንና ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮቹ ገልጸዋል።



ነገር ግን ይሄ ሁሉ ጉዳት መድረሱና የንጹሃን ህይወት ማለፉ እየታወቀ አንድም አካል ግን ስለጉዳዩ ማንሳት አለፍለገም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page