በሰሜን ሸዋ በሸዋሮቢትና በአካባቢው ንጹሃን ዜጎች ላይ የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል በከፈተው ተኩስ በትንሹ ወደ 10 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 አስታወቁ።
ትላንትን ያሳለፉት በከባድ ሁኔታ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ይሄው ቡድን ቀኑን ሙሉ በከባድ መሳሪያ ሲደበድባቸው መዋሉን ነው የሚናገሩት።
በዚህ ጥቃት በትንሹ ወድ 10 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን ነው ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 የገለጹት።
የሚያሳዝነው የእርስ በርስ መገዳደልን ፈጥረው በንጹሃን መገደል ለምንድን ነው የሚደሰቱት ሲሉም ይጠይቃሉ።
ዛሬ ጥቃቱ ጋብ ያለ ቢመስል ነገር ግን ይሄ ቡድን ሃይሉን እየጨመረና ወደ አካባቢውም እየተጠጋ መሆኑን ይናገራሉ።
ነገር ግን ይሄ ገዳይ ቡድን ራሱን ችሎ ሳይሆን በአካባቢው ሆድ አደር የብአዴን ካድሬ እየተመራ ነው ንጹሃንን እየፈጀ ያለው ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በዚሁ ገዳይ ቡድን የተተኮሰው ካባድ መሳሪያ በጫሬ 03 ቀበሌ የሚገኘው የውሃ ታንከር ከጥቅም ውጪ አድርጎታል ብለዋል።
ይሄን ተከትሎም ከተማዋ ከውሃ አገልግሎት ውጪ እንድትሆን አድርጓታል ሲሉም ለኢትዮ 360 ገለጸዋል።