top of page

ከቶ ማን ነው ህገ ወጡ?

የኦሮምያ ክልል መንግስት አዲስ አበባ ላይ ቤተ መንግሥት እሰራለሁ ብሎ ቢሊዮን ብሮች መድቧል። በአንድ በኩል የኦሮሞ ህዝብ ስንት ፈጥኖ ደራሸ እርዳታ በሚፈልግበት በዚህ ሰአት የክልሉ መሪ ቅንጡ ቤተመንግስት ለመገንባት መነሳቱ አንድ አሳዛኝ ታሪክ ነው።


በጣም የሚገርመው ነገር ግን ይህ የቤተመንግስት ግንባታ ህገ ወጥ መሆኑ ነው። የኦሮምያ መንግስት አዲስ አበባ ላይ ቤተ መንግሰት ለመስራትም ሆነ መቀመጫውን ለማድረግ የሚያስችለው አንድም ድንጋጌ የለም። በፌደራሉ ህገ መንግስትም ይሁን በኦሮምያ ህገመንግስት ውስጥ አዲስ አበባ የኦሮምያ ክልል መቀመጫ ናት የሚል ድንጋጌ የለም። የተሻሻለው የኦሮምያ ህገ መንግስትም አዲስ አበባ ዋና ከተማዬ ናት አይልም። ለነገሩ የኦሮምያ ክልል ህገ መንግስት ይህንን ለማለት ቢነሳም ከዋናው ህገ መንግስት የሚቀዳ ስለማይሆን ውድቅ ይሆናል። የሆነ ሆኖ ግን አንድም ሰነድ አዲስ አበባ የኦሮምያ ዋና ከተማ ናት የሚል የለም።


በዚህ ሰአት ፌደራል መንግስት አዲስ አበባን መቀመጫው ሲያደርግ ድንጋጌዎች አሉት። በፌደራል መንግሥት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር መካከል ህጋዊ መተሳሰር አለ። ትስስሩ መሻሻል እንዳለበት የሚታወቅ ቢሆንም።


ነገር ግን በኦሮምያና በአዲስ አበባ አስተዳደር መካከል ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ አንድም ትሰሰር የለም። በዚህ መሰረት የኦሮምያ መንግስት አዲስ አበባ ላይ የተቀመጠው ህገ ወጥ ሆኖ ነው። ግንባታዎቹ ህገ ወጦች ናቸው። ይልቅ እነዚህ ህገ ወጥ ቤት ሰርታችኋል የሚባሉት እና ቤታቸው የሚፈርስባቸው ወገኖች ይልቅ እነሱ ከገበሬው መሬት ያዛወሩበት ሰነድ አላቸው። ደግሞም መንግስት የቤት ፍላጎቶችን ማሟላት ስላልቻለ ጎጆ ቀልሰው የሚኖሩ ዜጎች ናቸውና ልንታገሳቸው የሚገባቸው ነበሩ።


አዲስ አበባ ላይ የኦሮምያ መንግስት ያለ ምንም ድንጋጌ ዋና ከተማዩ እያለ ሲኖር፣ ግንባታ ሲያካሂድ፣ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ሽፋን ይሰጣሉ። ለነገሩ እኚህ ሴት ከንቲባ የሆኑትም ለዚህም ነው። ወይዘሮ አዳነች በአንድ ወቅት ህገ መንግስታችን አዲስ አበባ የኦሮምያ መቀመጫ ናት ይላል ብለው የሃሰት መረጃ ሰጥተው አልተጠየቁም። አዲስ አበባ የኦሮምያ ዋና ከተማ ናት የሚል በሀገራችን ሰማይ ስር አንድም ህግ የለም ጎበዝ።


ከሁሉም ከሁሉም የልየሚያሳዝነው ግን ፓርላማውም ይሁን የአዲስ አበባ ምክር ቤት የኦሮምያን ክልል መንግሰት ለመሆኑ በየትኛው ድንጋጌ ነው አዲስ አበባ መቀመጫዬ ናት የምትለው? ድንጋጌ አምጣ፣ ስነድ አምጣ፣ ብሎ አለመጠየቁ ነው። የጉድ ሀገር......ከማለት ሌላ ምን ይሏል?


አዲስ አበባ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት መሆኗ ተከብሮ ደግሞ የኦሮምያ ክልል መቀመጫ አዲስ አበባ ይሁን ከተባለ ስምምነትና ድንጋጌ ያስፈልጋል እኮ። የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የኦሮምያ ክልል የሚተሳሰሩበት ግልጽ ዶክመንት ያስፈልጋል እኮ። አገርን የሚያስተዳድር ሰው እንዴት ህገ ወጥ ስራ በዚህ ደረጃ ይሰራል?


ወገኖቼ ሆይ በዚህ ሰአት የኦሮምያ መንግስት እንቅስቃሴ አዲስ የአበባ ላይ ህገ ወጥ ነው። ሁላችንም ተባብረን ህግ ይከበር እንበል። አሰራርና ህግ ይኑር። እባካችሁ ህግ ይከበር!

Recent Posts

See All

ነሃሴ 18/2015 በሰሜን ሸዋ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ /መኮይ/ ገና በጠዋቱ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። ገና ሳይነጋ ንጹሃንን ሊፈጅ ወደ በአንጾኪያ...

ነሐሴ 18/2015 የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ገለጹ።

በደቡብ ክልል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ክልል ውስጥ ያሉው የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ። አዲስ ተቋቋመ በተባለውና ከፍተኛ ቁጥር...

Comments


bottom of page