top of page

ኢትዮ 360 -ግንቦት 9/2015) ከኦሮሚያ ክልል ትጥቅ ፈቷል በሚል የተደራጀ አዲስ ሃይል ወደ አዲስ አበባ ገባ።


ከኦሮሚያ ክልል ትጥቅ ፈቷል በሚል የተደራጀ አዲስ ሃይል ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።


ይሄ ህገወጥ ስብስብ ትጥቁን ፈቷል በሚል የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ የማድረጉን ስራም አስቀድሞ ሲሰራ መቆየቱን ይናገራሉ።


እናም በገፍ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ ከተደረገው ከዚህ ቡድን ውስጥ የተወሰነው የመከላከያን ልብስ እንዲለብስ፣ከፊሉ ደግሞ የፌደራል ፖሊስን ልብስ እንዲለብስ ሲደረግ አብዛኛው ግን ለሌላ ተልእኮ ተዘጋጅቶ በከተማዋ እንዲቆይ መደረጉንም ምንጮቹ ጠቁመዋል።


እነዚህ ወደ ተለያዩ የጸጥታ አካል ውስጥ የተቀላቀሉትንም ከዚህ በፊት በሌሎች እና የእነሱም ሆነው አይታመኑም በሚባሉ አመራሮች ቦታ እንዲተኩ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።


ይሄ ቡድንን ጨምሮ አስቀድሞ ወደ ከተማዋ እንዲገባ የተደረገው የኦነግ ገዳይ ቡድን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ መሳሪያ ይዞ እንዲንቀሳቀስ መደረጉንም አመልክተዋል።


የአማራውን ጨምሮ የሌላ ብሔር የጸጥታ ሃይል ስምሪቱን ዱላ ይዞ እንዲወጣ ሲያደርግ ይሄ ህገወጥ ቡድን ግን በኪሱ ሽጉጥ ሳይቀር እዲታጠቅ ተደርጓል ብለዋል።


ይሄ ወደ ከተማ እንዲገባ የተደረገው ህገወጥ ቡድን በተለይ በአካኮ፣ በእንጦጦ ፣ በቡራዩና አካባቢው የደቡብ ሕዝቦችን በማፈናቀል፣ በአዲስ አበባ ሽሮሜዳ የባህላዊ አልባሳትን በተለይ ደግሞ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ልብስ እንዳይሸጥ በመከልከል የእሁድ ገበያን ባዶ አድርጎታል ይላሉ።


ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ድምቀትም የሆነውን ባህላዊ አልባሳትን የሚጠበቡበት የጋሞ ህዝቦችና በንግዱ አለም ድምቀት የሆነውን የጉራጌ ማህበረሰብ በማፈናቀልና በመግደል ከአዲስ አበባና ዙሪያዋ እያጸዱት ነው ሲሉም ምንጮቹ ገልጸዋል።


ይሄው ቡድን በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን በማፈኑ በኩልም የተሰጠውን ተልእኮ እያስፈጸመ ነው ብለዋል የኢትዮ 360 ምንጮች።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page