በደቡብ ጎንደር ሰዴ ሙጃ ወረዳ ላይ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላት የገደለውና ያቆሰለው የአካባቢው ሚሊሻና የኦህዴዱ ሃይል አሁንም ከተማዋን መክበባቸውን የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ከአንድ ቀን በፊት የአካባቢው ሚሊሻና የኦህዴዱ የመከልከያ ሃይል በጋራ በከፈቱት ጥቃት 7 የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላትን ሲገሉ 11ንዱን አቁስለዋል ብለዋል።
በሶስት ቀበሌዎች ጥቃት የተፈጸመባቸው የፋኖ ህዝባዊ አባላቱ የተገደሉትና የቆሰሉት ህብረተሰቡን አደራጅተው የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት እንደሆነም አመልክተዋል።
ይሄንን ተግባር የፈጸመው ገዳይ ቡድን ሃይል ከየአካብቢው በማስመጣት ጭምር ከተማዋን በድጋሜ አስከብቧታል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።