በኮምቦልቻ የኦህዴዱ ጄነራሎች በሚስጥር እየመከሩ መሆኑን የኢትዮ 360 የአካባቢው ምንጮች ገለጹ።
ይሄ የጄኔራሎቹ ስብሰባ ቀናትን የወሰደ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቹ ሚስጥራዊ ስብሰባው እየተካሄደ ያለው ደግሞ ሰን ሳይድ በሚባለውና የኦህዴዱ ገዳይ ቡድን መሰባሰቢያ ነው በሚባለው ሆቴል መሆኑንም ይናገራሉ።
በሆቴሉ ያሉ ክፍሎችን ሁሉ አዘግቶ በሚስጥር እየመከረ ያለው ይሄው የኦህዴዱ ጄኔራሎች ስብስብ የጀመረውና ወደ አማራ ክልል የላከው ሃይሉ ሽንፈትን መከናነቡን ተከትሎ ነው ይላሉ።
አብይ አህመድ በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ሊፈጽም ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል አለመሳካቱን ተከትሎ አዲስ ዘመቻ ለመክፈት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።
ቀናትን የወሰደው የኦህዴዱ ጄኔራሎች የሚስጥር ስብሰባም የዚሁ አንድ አካል መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ሚስጥራዊ ስብሰባው መቼ እንደሚጠናቀቅ ባይታወቅም ነገር ግን ከዚህ ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ በሁሉም አቅጣጫ ከበንዋል ብለው በሚያስቡት የአማራ ህዝብ ላይ አዲሱን የማጥቃት ዘመቻ ሊጀምሩ ይችላሉ ሲሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
በዚህ ምስጥራዊ ስብሰባ ላይ ደግሞ ተልእኮ የሚሰጣቸው የብአዴን ብልጽግና ካድሬዎች መኖራቸውንም ነው የኢትዮ 360 የአካባቢው ምንጮች የሚናገሩት።