(ኢትዮ 360-ግንቦት 3/2015) በአማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደው አፈና እስከጾታዊ ጥቃት የደረሰ መሆኑ ተገለጹ።
በአማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደው አፈና እስከጾታዊ ጥቃት የደረሰ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በአዲስአበባ ላፍቶ ገብርኤል አካባቢ የሥራ ቦታዋ ድረስ ተከታትለው የሔዱ ፖሊሶች እጅግ አስነዋሪ በሆነ መንገድ አግተው የወሰዷት ጋዜጠኛ ገነት አስማማው አፈና ይሄንን በግልጽ የሚያሳይ ነው ይላሉ ምንጮቹ።
የአፈና ሒደቱን በስልክ ለወዳጆቿ በቀጥታ ስታስተላለፍ የነበረውንም መረጃ ያስታውሳሉ ምንጮቹ።
ጋዜጠኛ ገነት የመንግስት ፀጥታ አካላት ነን ያሉ የአፋኝ ቡድን አባላት ክብረ-ነክ በሆነ መንገድ ሲሳድቧት እና ሲዘልፏት፡ ለአለም አደባባይ ደርሶ መሰማቱም ያስታውሳሉ።
የአፋኝ ቡድኑ አባላት ጋዜጠኛ ገነት አስማማውን እየተሳደቡ ፣ እየጎነተሉ ፣ እየጎተቱ ከሕንፃው ይዘዋት ሲወጡ በሕንፃው የCCTV camera ተቀርፆ እንደነበር ይጠቁማሉ።
ሆኖም በስልክ የተገለጠው ገመናቸው በምስል የሚገለጥ መሆኑ ያሳሰባቸው የአፋኙ ቡድን ሹማምንት፡ የሕንፃው ባለቤቶችን በማስፈራራት ያ ፊልም ከማሕደር እንዲጠፋ ማድረጋቸውንም ምንጮቹ ያጋልጣሉ
የጋዜጠኛ ገነት አስማማውን አያያዝ በተመለከተ በድምፅ መረጃ ከተሰማ በኋላም እነዚያው ጋጠወጥ የአፋኝ ቡድኑ አባላት የፆታዊ ጥቃት ሙከራ እንዳደረጉባት ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የያዟት ፖሊሶች ከመሳደብ ጋር ፆታዊ ትንኮሳ አድርገዋል\ የሚሉት ምንጮቹ፣ ሴትነቷን ለማዋረድ እና ለመድፈር ሞክረዋል ሲሉም አንስተዋል።
እሥር ቤቶችን ለጎበኙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሙያተኞች፡ ያለው መአጃ ሁሉ እንዲደርሳቸው ቢደረግም የኮሚሽኑ ሙያተኞች ግን በሪፖርታቸው ጉዳዩን ሳያነሱት አልፈዋል ሲሉ እየተሰራ ያለውን ወንጀል ያጋልጣሉ።
የኦህዴዱ አፋኝ ቡድን አባላት የአማራ ልጆችን በሚይዙበት ወቅት የሚያሳዩት ንቀትም ሆነ ጥላቻ ለሰው ልጅ የተሰጠውን የሰብአዊ መብት የሚጥስና የጸጥታ ሃይል ነኝ የሚለውን ቡድን የወረደ ሰብእና የሚያሳይ ነው ሲሉም ያነሳሉ።
ከገነት አስማማው ሌላ እነ ጋዜጠኛ ጎአበዜ ሲሳይም ሲታፈኑ በተመሳሳይ እንግልትና ድብደባ መፈጸሙን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ጋዜጠና ጎበሴ ሲሳይ ላይ "ይሔ መንግስት የኦነግ መንግስት ነው ትላላችሁ፣ አዎ! የኦነግ መንግስት ነው!! ምን ታመጣላችሁ? አንድ ነገር ቢመጣ ያላችሁበት ድረስ ገብተን እንገላችኋለን!" በሚል ሲዝት የነበረው አካል ዶ/ር ቀለምወርቅን በጨለማ ቤት ስድስት ቀን አግቶ ሲዘልፋቸ3ውና ሲሰበድባቸው መቆየቱን ያነሳሉ።
ዶ/ር ወንደሰንም በተመሳሳይ ፍርድ ቤት እንዳይቀብ ተደርጎ ለአራት ቀናት አይኑን ተሸፍኖ በሰንሰለት ታስሮ እንዲቆይ መደረጉን በማሳያነት ያቀርባሉ።
ይሄ ሁሉ በደል እየተፈጸመባቸው ያለው ጋዜጠኛ ገነት እና ሌሎች የአማራ ጋዜጠኞች ቀድመው በተከሰሱበት ጉዳይ ፍርድ ቤት በዋስትና መብት ከእሥር ቤት እንዲወጡ ቢፈቅድም፡ የኦህዴዱ አነግ አገዛዝ ግን ከህግ በላይ ሆኖ አግቶ አስቀምጧቸዋል ብለዋል።