top of page

(ኢትዮ 360 -ግንቦት 2/2015) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ሆነች ህዝቡ በፈተና ውስጥ እያለፉ ነው።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደቤተክርስቲያን ህዝብም እንደህዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው ሲሉ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አስታወቁ።


ቅዱስ ፓትሪያርኩ ይሄን ያሉት በቤተክርስቲያኗ ቀኖና መሰረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በ25ተኛው ቀን የሚካሄደውን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግራቸው ነው።


የቤተክርስቲያናችንም ሆነ የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል ሲሉም በንግግራቸው አሳስበዋል።


ቤተክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣ በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የሚታዩ ጉዳዮች መኖራቸውንም ቅዱስ ፓትሪያርኩ በንግግራቸው አስምረውበታል።


በተለይም በትግራይ እና በኦሮምያ አካባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል ሲሉ አመልክተዋል።


እኛ ያጐደልነው ፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።



በተፈጠረው አላስፈላጊ ከባድ ጦርነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተፈናቀሉ ምእመናን ልጆቻችንን በፍጥነትርሰን የምናጽናናበትንና የምንደግፍበትን ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ማየት ይኖርብናልም ብለዋል።


ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት ውይይቱን በቀጠለበት ሁኔታ ውስጥ በነአብይ የተላከው የኦህዴዱ ሃይል ደግሞ በቅርብ እርቀት ቤተክህነቱ ላይ አነጣጥሮ እንደሚገኝም የኢትዮ 360 ምንጮች ጠቁመዋል።


እነሳውሪዎስ ከነሽመልስ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት ሲኖዶሱን ለመበጥበት ሰሞኑን ሲያደርጉት የነበረውን ሙከራ በዚህ ምልአተ ጉባኤ ላይም ለመድገም ተዘጋጅተዋል ሲሉ ይናገራሉ።


በነሽመልስ አብዲሳ የተቋቋመውና ሲኖዶሱን ሙሉ በሙሉ ለመሰልቀጥ የተዘጋጀው ቡድንም ምልአተ ጉባኤውን ለመበጥበጥ ተዘጋጅቷል ሲሉ ምንጮቹ አስጠንቅቀዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page