top of page

ኢትዮ 360-ግንቦት 2/2015) በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ሞቶ የተገኘው ተማሪ ጉዳይ አነጋጋሪ ነው።


በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ራሱን በመስቀል ሕይወቱን አጥፍቷል በሚል ከዩኒቨርስቲው የወጣው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ የዩኒቨርስቲው የውስጥ ምንጮች ለኢትዮ 360 ገለጹ።


የአንደኛ አመት የሶሻል ሳይንስ ተማሪ የሆነው አበባው ስንሻው ከሶስት ቀን በፊት በዶርሙ የእጅ ስልኩን ቻርጀር ላይ አድርጎ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄዱን ለጓደኞቹ ነግሮ ከሄደ በኋላ አለመመለሱን ይናገራሉ።


ግራ የገባቸው ጓደኞቹም ለዩኒቨርስቲው አስተዳደር ጓደኛው እንደወጣ አለመመለሱን ገልጸው እንዲጣራላቸው መጠየቃቸውን ተናግረዋል።


ነገር ግን ከዩኒቨርስቲው የተሰጣቸው ምላሽ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያለውን ካሜራ ተመልክተን ምላሹን እንሰጣችኋለን የሚል ቢሆንም ያን ግን ማድረግ አልቻሉም ይላሉ።


ከሞተ ከሶስት ቀን በኋላ አስከሬኑ የተገኘው ተማሪ አበባው ስንሻው ፈተና ከበደኝ በሚል ሲጨናነቅ ነበር በሚል ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የወጣውም መረጃ በፍጹም ከእውነት የራቀ ነው ይላሉ።


ለዚህ ማሳያው ደግሞ ተማሪ አበባው በየትኛውም የትምህርት አይነት ላይ ከበደኝ የሚል ሮሮ ሲያሰማ አይተው አለማወቃቸው መሆኑንም አመልክተዋል።


ነገር ግን ተማሪ አበባው ዘወትር የሚጠቀመው በዛው በዶርም ውስጥ ያለውን መጸዳጃ ቤት ሆኖ ሳለ አስከሬኑ ግን ተገኘ የተባለው ከዶርሙ ውጪ ባለና ቆርቆሮ በቆርቆሮ በተሰራው መጸዳጃ ቤት ውስጥ መሆኑን ያነሳሉ።-ለሶስት ቀናት አስከሬኑ በዛ መቆየቱን በመናገር ጭምር


ይሄ ብቻ ሳይሆን ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የጓደኛቸው መሰወር አሳስቧቸው ለዩኒቨርስቲው አቤት ሲሉ ለቆዩት ጓደኞቹ ምላሽ የከለከለው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ከሶስት ቀን በኋላ ያልተለመደ አይነት የሃዘን መግለጫ በማውጣት ጭምር የተማሪውን ሞት ለማደባበስ የሄደበት ርቀት በራሱ አጠራጣሪ ነው ብለዋል።


በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ሁሌም ይቆጨውና በተቻለው አቅም ሁሉ ለተጎዱ ወገኖቹ ድምጽ ለመሆን ሲሞክር የነበረው ተማሪ አበባው ስንሻው ራሱን አጥፍቶ ሳይሆን ሆን ተብሎ ተገሏል ሲሉም የዩኒቨርስቲው የውስጥ ምንጮች እውነታውን ያጋልጣሉ።


የተማሪው በዚህ መልኩ ሞቶ መገኘት ያበሳጫቸው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ለመውጣት ቢሞክሩም የጠበቃቸው ግን አስለቃሽ ጭስና ድብደባ መሆኑንም የውስጥ ምንጮቹ ይናገራሉ።


ግቢው ውስጥ በመግባት ጭምር ይሄንን ሁሉ ድብደባና ማሳደድ ሲፈጸም የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ዝምታን መምረጡንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


የዩኒቨርስቲው የውስጥ ምንጮች አሁንም የተማሪ አበባው ገዳይ በትክክል ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ካልተደረገ በቀጣይም በዚህ መልኩ ህይወታቸውን የሚያጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችልም ከወዲሁ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page