top of page

(ኢትዮ 360-ግንቦት 1/2015)ከአማራ ልዩ ሃይል ተርፎ የነበረው ሃይል ከነትጥቁ ጠፋ።


የአማራ ልዩ ሃይል ሲበተን ስልጠና ትወስዳላችሁ በሚል ተመዝግበው ከነበሩት የልዩ ሃይል አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ዛሬ ከነትጥቃቸው መጥፋታቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


ሰማንያ በመቶ የሚሆነው የአማራ ልዩ ሃይል ሲበተን የተወሰነው ሃይል ከኦህዴዱና ከብአዴኑ ካድሬ የቀረበለትን ሽንገላ ሰምቶና ስሙን አስመዝግቦ መቅረቱንም ኢትዮ 360 በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።


ይሄ ከዋናው ልዩ ሃይል ተነጥሎ ቀርቶ የነበረው ስብስብ አስቀድሞ የተነገረው ለአዲስ ስልጠና ወደ ማሰልጠኛ ትገባለህ የሚል እንደነበርም ያነሳሉ።


ቀሪው ልዩ ሃይል ስሙን ሲያስመዘግብ ስልጠና የሚገባበትም ቀን ግንቦት 1 መሆኑ ተነግሮት እንደነበርም ምንጮቹ ገልጸዋል።


እናም በተባለው መሰረት ዛሬ ደሞዙ እንዲከፈለው የተደረገው ልዩ ሃይል ወደ ስልጠና የምትገባው መሳሪያህን አስረክበህ ነው የሚል ትእዛዝ እንደወረደለትም ይናገራሉ።


ይሄንን ከሰማው ልዩ ሃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጥ ከነመሳሪያው መበታተኑን ይናገራሉ።


ይሄንን ሃይል አሳዶ ለመያዝ ሲሞከር ደግሞ ልዩ ሃይሉ በተለያየ አቅጣጫ በመበተኑ አስቸጋሪ ሆኗል ይላሉ።


የተለያዩ ድለላዎችን ሲያቀርብ የነበረውና በገዛ ወገኑ ላይ ጥይት እንዲስብ ለማድረግ የመጨረሻውን ስልጠና ሊሰጥ የተዘጋጀው ሃይል ልዩ ሃይሉ ከነመሳሪያ በመጥፋቱ ሳይሳካለት ቀርቷል ብለዋል።


አሁን በእጁ የቀሩት የልዩ ሃይል አባላት በጣት የሚቆጠሩ ያህል መሆናቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ከጅምሩ ከነመሳሪያ የተበተነው ልዩ ሃይል ጉዳይ ጭንቅ ሆኖበት የነበረው የኦህዴዱ ብአዴን ስብስብ አሳምኜዋለሁ ያለው የልዩ ሃይል ዛሬ ከነትጥቁ መበታተኑ ደግሞ ከባድ ድንጋጤን ፈጥሮበታል ብለዋል።


በየአካባቢው በሽማግሌና በሃይማኖት አባት ስም ካድሬዎቹ እየላከ የአማራውን የህልውና ትግል ለመጎተት እየጣረ ያለው የኦህዴዱም ሆነ የብአዴኑ ሆድ አደር ቡድን በየትኛም በኩል እቅዱ ሊሳካለት አልቻለም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


ከመከላከያና ከፌደራል ሃይል ስልጠና ልትገባ ነው በሚል መሳሪያቸውን እየተነጠቁ ወደ ማጎሪያ ከሚወሰዱት የአማራና የደቡብ ተወላጆች ውጪ ወደ አማራ ክልል ወገናቸውን ለመውጋት ከሚላኩት አብዛኞቹ የመሳሪያቸውን አፈሙዝ ወደ ገዳዩ ቡድን እያዞሩ መሆኑን ነው ምንጮቹ የሚናገሩት።


ከነዚህ መካከል ደግሞ ሌላ ተልእኮ ተሰቷቸውና የስለላ መሳሪያ ተገጥሞላቸው ከገቡት ውጪ አብዛኛው ግን ወገኔን አልወጋም በሚል አቋሙ መጽናቱንም ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የተናገሩት።


ሰሜን ሸዋን ጨምሮ ወደ ጎንደር ጎጃምና ወሎ እየተጋዘ ያለው የኦህዴዱ ሃይል ለተጨማሪ ጥቃት ምሽግ እየቆፈረና ራሱን ለሌላ የዘር ማጥፋት ወንጀል እያዘጋጀ መሆኑንም ነው ምንጮቹ ጨምረው የገለጹት።


የአማራ ክልልን በሁሉም ያስከበበው አብይ አህመድ የአማራ ህዝባዊ ሃይልንም ሆነ ንጹሃን ዜጎችን ለመጨረስ የያዘውን እቅድ ለማሳካት ያለውን ሃይል በሙሉ እየተጠቀመ መሆኑንም አመልክተዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page