top of page

(ኢትዮ 360-ግንቦት 1/2015) በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ ተገኘ።

(ኢትዮ 360-ግንቦት 1/2015) በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ ተገኘ።


በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ከባድ ተቃውሞ መቀስቀሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


እስካሁን ድረስ ማንነቱ ያልታወቀውና በምን እንደሞተ ያልታለየው ተማሪ ከሞጣ አካባቢ የመጣ መሆኑ ብቻ መረጋገጡን ያስቀምጣሉ።


የተማሪው ሞቶ መገኘት ያስቆጣቸው ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት መጀመራቸውን ያነሳሉ።


ነገር ግን ተማሪዎቹ የተቃውሞ ድምጻቸውን ገና ማሰማት ሲጀምሩ በአካባቢው የደረሰው የጸጥታ ሃይል በአስለቃሽ ጭስ እንዲበተኑ ማድረጉን ይናገራሉ።


በአስለቃሽ ጭሱ አልበተን ባሉ ተማሪዎች ላይ ደግሞ ከባድ ድብደባ መፈጸሙንም ነው ምንጮቹ የሚናገሩት።


ከነዚህ መሃልም በዚሁ የጸጥታ ሃይል የታፈኑ ተማሪዎች መኖራቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

አብዛኛው ተማሪ ሸሽቶ ወደ ሴቶቹ ዶርም ቢያመራም የጸጥታ ሃይሉ ግን ተማሪውን ከማሳደድ ወደ ኋላ አለለም ብለዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ አመት የሶሻል ሳይንስ ተማሪ የሆነው አበባው ስንሻው በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ራሱን ሰቅሎ ገሏል ሲል ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።


ዩኒቨርስቲው ባልተለመደ መልኩ አወጣሁት በላው የሃዘን መግለጫ የተማሪ አበባውን አሟሟት በተመለከተ ተጨማሪ ምርመራ ቢያስፈልግም ተማሪ አበባው ግን ፈተና ከበደኝ በሚል ሲጨናነቅ እንደነበር መረጃ አግኝቻለሁም ብሏል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page