በባህርዳር ወጣቶች በለሊት ሁሉ ከቤታቸው እየተወሰዱ በሰው በላው ሃይል በአደባባይ እየተረሸኑ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ይሄንን ወንጀል ለመፈጸም ደግሞ የደህንነት ቡድኑን እንዳሰማራም ይናገራሉ።
የብአዴኑ ሆድ አደር ቡድን ደግሞ ገዳይ ቡድን በማስገባት የራሱን ህዝብ ማስጨረሱን አለም ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ብለዋል።
ሰሞኑን በባህርዳር ይሄው ገዳይ ቡድን የባንክ የጥበቃ ሰራተኞችን አንበርክኮ እስከመግደልና ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችንም ጨፍጭፏቸዋል ሲሉም የተሰራውን የጦር ወንጀል ያጋልጣሉ።
በግፍ የተገደሉ ወገኖቻቸውን እስከ ትላንት ምሽት ሲቀብሩ ማምሸታቸውንም ገልጸዋል።
በቀበሌ 14 ብቻ በዚሁ ቡድን የተገደለው የአማራ ተወላጅ ቁጥር ከ50 በላይ እንደሚሆን ይናጋራሉ።
በቱቦ ውስጥ ሁሉ ተጥለው የተገኙ ወገኖቻቸውን የገደለው ቡድን በአደባባይ እያነጣጠረ ቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን ንጹህ አማራ ሁሉ ተገሏል ብለዋል።
እጁ ላይ ምንም መሳሪያ ያልያዘን ንጹሃን ዜጋን እየገደለ ያለው ቡድን አንድም የህዝባዊ ሃይሉን አባል ግን ማግኘት አልቻለም ሲሉ የህዝባዊ ሃይሉን ጀግንነት ይመሰክራሉ።
ከዛም አልፎ ዘመን ካሴን አገናለሁ ብሎ የገባው ይሄው ቡድን ቤት ለቤት ዝርፊያ ላይ መሰማራቱንም ተናግረዋል።
ንብረታችንን አናዘርፍም ያሉ ሰዎች በቤታቸው ተገለዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ ከአንድ ቤት ብቻ 6 አስከሬን መውጣቱንም በሃዘኔታ ተናግረዋል።
በገፍ እየገባ ያለውን ገዳይ ቡድን ህዝባዊ ሃይሉ አይቀጡ ቅጣት ቀቶታል ሲሉ ያዩትን ይናገራሉ።
በጅግንነቱ መቋቋም ያልቻሉትን ህዝባዊ ሃይል ማግኘት ያልቻለው ይሄው ሰው በላ ሃይል ንጹሃንን እየጨረሰ ነው ብለዋል።
በወይዘሪት ፍሬህይወት የሚመራው ኢትዮ ቴሌኮ ደግሞ የአማራ ክልልን ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ በማድረግ ንጹሃንን እያስጨፈጨፈ መሆኑንም ያመለክታሉ።
አሁን ላይ ባህርዳር ላይ ያለው ውጊያ ጋብ ያለ ቢመስልም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይሉ ከያዘው አራት ታንክ ጋር ወደ መርሃዊ እየገሰገሰ መሆኑም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በባሕርዳር ሴቶችን መድፈርና እና መዝረፍ አይን ባወጣ መልኩ መጀመሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
የሚታፈኑ ወጣቶችን እያፈነ ወደ መኮድ ኣያጋዘ ያለው ቡድን ምናልባትም እነዚህ ወጣቶችን ሊረሽናቸው ይችላሉም ሲሉም ነው ምንጮቹ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
በመኮድ አካባቢ አልፎ አልፎ የተኩስ ደምጽ የሚያሰማው ይሄው ቡድን በየቤቱ የጀመረውን ከተራ ሞባይል እስከ ገንዘብ ዝርፊያውን ቀጥሏል ብለዋል።
ስራ ጀመረ የተባለውም አየር መንገድ የወጣቶች ማጥመጃ ሆኗል ሲሉም እውነታውን አስቀምጠዋል።
ወደ አየር መንገዱ የሚጓዙ መንገደኞች ደግሞ ወዴትም መንቀሳቀስ አትችሉም በሚል ከዛው እየታፈኑ ወደ መኮድ እየተጋዙ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።