top of page

ኢትዮ 360 - ነሀሴ 10/2015) በናዝሬት ከተማ በህጋዊ መንገድ መሳሪያ የያዙ ነዋሪዎች መሳሪያቸውን እየተነጠቁ ነው።


በናዝሬት ከተማ በህጋዊ መንገድ መሳሪያ የያዙ ነዋሪዎች መሳሪያቸውን በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ መመሪያ መውረዱን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።


ቀደም ሲል ይላሉ ምንጮቹ የግል መጠበቂያቸው የሆነውን የጦር መሳሪያ ህጋዊ ፍቃድ እንዲያወጡ ይሄው አካል መመሪያ ማውረዱን ተከትሎ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች መሳሪያቸውን ማስመዝገባቸውን ይናገራሉ።


በተለያዮ የፖሊስ ጣቢያዎች በመገኘት ህጋዊ ፈቃድ ማውጣታቸውን ያስታውሳሉ።


ነገር ግን አሁን በህጋዊ መንገድ መሳሪያ የያዙ በሙሉ ቤታቸው ድረስ ስልክ በመደወል ጭምር መሳሪያቸሁን ከነፈቃዱ አስረክቡ በሚል እየተዋከቡ ነው ብለዋል የኢትዮ 360 ምንጮች።


በዚህ ውስጥ ደግሞ በአብዛኛው መሳሪያ አስረክብ እየተባለው ያለው የአማራና የሌላው ብሄር ሲሆን ባለጊዜ ናቸው የተባሉት ግን ሊያስረክቡ የወሰዱትን መሳሪያ ይዘው እንዲመለሱ እየተደረጉ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


አማራውንና ሌላውን ብሔር ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል ወከባ እየፈጠረ ያለው የከተማው አስተዳደር በጎን በኩል ከከተማው ውጪ ለመጡ የባለጊዜው ህገወጥ የወጣቶች ስብስብ በድብቅ ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ኢትዮ 360 ትላንት ባወጣው መረጃው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።


ከአማራውና ከሌላው ብሔር ላይ እየተነጠቀ ያለው መሳሪያ ደግሞ ለዘር ማጥፋት ወንጀል ለተዘጋጁ የገዳዩ ቡድን ስብስቦች እየታደለ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


አሁን በከተማው እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በቀጣይ ሊፈጸም ለታሰበው የዘር ፍጅት ቅድመ ዝግጅት ነው ሲሉም መሬት ላይ እየታየ ያለውን እውነታ አስቀምጠዋል።


አሁን በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ በናዝሬትና አካባቢው የታቀደውን የዘር ፍጅት አስቀድሞ ማስቆም ካልቻለ በቀር መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page