በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው አፈና በሚያሳዝንና በአስከፊ ሁኔታ ቀጥሏል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
የአማራ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶችን በብሔራቸው በመለየት ብቻ አፈናውን ሲቀጥል ለሰው በላው ስርአት አስጊና የህዝቡ አይን ናቸው የሚባሉ ወጣቶችን ከየአካባቢው እያፈነ መሆኑን ተናግረዋል።
ኦቪድ በየአካባቢው የሚያስገነባቸው የማጎሪያ ስፍራዎች ከመሙላት አልፈው የንጹህ መገደያም ወደ መሆን ተሸጋግረዋል ሲሉም ያነሳሉ።
በየአካባቢው ያገኘውን ወጣት ሁሉ እያፈነ ወዳልታወቀ ስፍራ የሚወስደው ይሄው አካል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ የግዥ ባለሙያነት የነበረውን እንዳልካቸው እሸቱን በተለያዩ ግዚ በእርስ ሲያሰቃየው አካል በመጨረሻም መርዞ ገሎታል ሲሉ ምንጮቹ ይናገራሉ።
ውልደቱ ወሎ ባቲ የሆነው እንዳልካቸው በተደጋጋሚ ጊዜ በአዳነች አበቤ ሲታሰር በአድዋ ድል በዓል ላይ የምኒሊክ ፎቶ ያለበት ቲሸርት ለብሰሃል፣ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት አስተላልፈሃል በሚል መሆኑን ያነሳሉ።
በመጨረሻም የፋኖ አባል ነህ በሚል ለ17 ቀናት የት እንደታሰረ ያልታወቀው እንዳልካቸው ለበአል በሚል ከታፈነበት ቢለቀቅም ባለፈው አርብ ግን ተመርዞ በቤቱ ሞቶ መገኘቱን ይናገራሉ።
አሁንም ወጣቱን በዚህ ደረጃ የሚያፍሰው አካል በተደጋጋሚ በእስር ሲማቅቅ ቆይቶ የተለቀቀውን የኢንጂነር መለሰ ደባስን ወንድምም ማፈኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።