በምስራቅ ጎጃም የመርጦ ለማርያምና አካባቢው ከገዳዩ ቡድን ነጻ ሲወጣ በሸዋ የመረሃቤቴ ሚዳ ህዝባዊ ሃይል ደግሞ በሰው በላው ቡድን ሃይልን በሽምቅ ውጊያ ሙትና ቁስለኛ እንዲሆን ማድረጉን የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ህዝባዊ ሃይሉ አዲስ ዘመቻ ሰርቶ ይሄን ገዳይ ቡድን ለማስወጣት በተዘጋጀበት ሁኔታ ውስጥ ገዳዩ ቡድን ከተማውን ለቆ መፈርጠጡን ይናገራሉ።
በከተማው ገዳይ ቡድኑን ሲያግዙና የገዛ ወገናቸውን ሲያስወጉ የነበሩ የሆድ አደር የብአዴን ስብስቦች ላይም የተወሰዱ አንዳንድ ርምጃ መኖራቸውንም አመልክተዋል።
ከለሊቱ 10 ተኩል ጀምሮ ነጻ የወጣችው የመርጦ ለማርያም ከተማም ሰአታትን ባልፈጀ ጊዜው ውስጥ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ እንድትመለስ ተደርጋለች ብለዋል።
አሁን ህዝቡ ነጻነቱን አረጋግጦ የመስቀል ደመራ በአልን ለማክበር ተዘጋጅቷል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ ሚዳ ላይ ለሊቱን በገዳዩ ቡድን ላይ የሽምቅ ርምጃ የወሰደው ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ይናገራሉ።
ከነሱ ወገን አንድ አባላቸው ሲሰዋና አራት የሚሆኑ አባሎቻቸው ሲቆስሉ ከገዳዩ ቡድን ግን አብዛኛው ሙትና የተወሰኑት ደግሞ ቁስለኛ መሆናቸውን ነው ለኢትዮ 360 የገለጹት።