የደብረታቦርና የደብረማርቆስ አካባቢዎች ከገዳዩ ስርአት አገዛዝ ነጻ መውጣታቸውን የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 አስታወቁ።
ደብረታቦር ላይ በተለይ ታንት ቀን ላይ ተጀምሮ የነበረው ጦርነት አመርቂ በሆነ ውጤት ደብረታቦርን መቆጣጠር ተችሏል ይላሉ።
መሳሪያ ከመማረክ ጀምሮ ገዳዩን ሃይል ወደ ወሎ እንዳያልፍ በማድረግ ጭምር ታሪክ ሰርተናል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ከወልቃይት ተነስቶ ወደ ወሎ ሊያልፍ የነበረው ይሄው ገዳይ ሃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀቷል ብለዋል።
የጦር መሳሪያዎችን ከመማረክ ጀምሮ የተሰራው ስራ አማራውን የሚያኮራ ነው ሲሉ ገልጸውታል።
አሁንም ሁሉም የአማራ ህዝብ ከፋኖ ህዝባዊ ሃይል ጎን በመቆም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
አሁንም ዳባት ከጎንደር መግቢያ አውራ ጎዳና ፣ ወደአጅሬ መውጫ መወርጠጭ፣ ወደ ደባርቅ መውጫ ፍየል መቃብር ፣ ወቅን አካባቢ ጭና ያለው የገዳዩ ቡድን መንገድ ለመዝጋት ሙከራ እያደረገ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ አካባቢውን ጸጥ አድርጎ የዋለው የደበረማርቆስ ህዝብና የፋኖ ህዝባዊ ሃይል በስተመጨረሻ ደብረማርቆስና አካባቢውን ከሰው በላው ስርአት ነጻ ማድረግ ችሏል ብለዋል የኢትዮ 360 ምንጮች።
ብሬና ጁቤን ነጻ ያወጣው የፋኖ ህዝባዊ ሃይልና የአማራ ህዝብ ጋሸና ላይ ጉዳት ለማድረስ ሲጓዝ የነበረውን የኦነግ ጦር የደብረታቦር ነዋሪ መንገድ በመዝጋት ጭምር እንዳይፈናፈን አድርጎት ማደርና መዋሉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
አሁንም የንጹሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ ያልሰለቸው ገዳይ ቡድን የጎንደር ከተማን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ጎጃም ላይም ድሉን የራሱ እያደረገ ያለው የአማራ ህብዝና ህዝባዊ ሃይሉ የአማራ ልዩ ሃይልን ልብስ የለበሰው ቡድንን ጭኖ የነበረን 2 ኦራል ተሽከርካሪዎችን መማረኩንም ይናገራሉ።
ጎንደር አዘዞ ላይም በተመሳሳይ እረሽን የጫነ ኦራል ተሽከርካሪም ገቢ ሆኗል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ትላንት ባህርዳር ላይ ከየወረዳው ስብስባ ተጠርተው ከነበሩ የፖሊስ አባላት መካከል ሃሳባችሁን አልቀበልም ብሎ የሞገተ አንድ የፖሊስ ሃይል በአደባባይ አድማ ብትና ነኝ በሚለው አካል መገደሉንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በአርማጭሆ ተሰማርቶ የነበረው የገዳዩ ስርአት ሃይል ለሊቱን ከነመሳሪያው ጠፍቶ ሲያድር ቁጥራቸውም ከ40 በላይ እንደሚሆንም አመልክተዋል።
በቡሬ ግንባርም በንጹሃን ላይ ጦርነት የከፈተው ገዳይ ቡድን ከህብረተሰቡና ከህዝባዊ ሃይሉ ጥሩ ምላሽ እየተሰጠው መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በወሎና በሸዋም ንጹሃንን በአደባባይ እየረሸነና በግልጽ ጦርነት ያወጀው አካል አሁንም በሆድ አደሮቹ የብአዴን ሰዎች መንገድ መሪነት የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ቀጥሎበታል ብለዋል።
ሰሜን ሸዋ ላይ አሁንም ህብረተሰቡን ለገዳዩ ስርአት አሳልፈው የሚሰጡ መሬት ሲዘርፉና ሲያዘርፉ የቆዩ እንደ ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ነኝ እንደሚለው ዳምጠው ተሰማ አይነት ሰዎች አሁንም ለአማራው ጠላት ሆነው ቀጥለዋል ብለዋል።
በተጨማሪም የቤተመንግስት ወይም የፓርቲ ነጋዴ እየተባሉ ከሚጠሩት ካሳሁን ምስጋናው ወይንም በቅጽል ስሙ ካሳሁን ካርሎስና በላይነህ ክንዴ ደግሞ ሃብታቸውን በማፍሰስ ጭምር የፋኖ ህዝባዊ ሃይልንና የአማራ ህዝብን አሳልፈው ለገዳዩ ስርአት ለመስጠት ቃል ገብተው ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ጠቁመዋል።
በተደጋጋሚ ወጣቱን በገንዘብ በመደለልና ገዳዩን ስርአት እንዳይቃወም በማድረግ ጭምር ስራ ሲሰሩ የቆዩት እነ ካሳሁን ካርሎስ አሁን ደግሞ ሃይል በማደራጀት የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን ለማስመታት ከስምምነት መድረሳቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።