top of page

(ኢትዮ 360 _ግንቦት 8/2015) በሲዳማ ክልል የተቋቋመው የሙስና ኮሚቴ ወንጀለኞችን እየደበቀ ነው።


በሲዳማ ክልል የተቋቋመው የሙስና ኮሚቴ ዋና በሌብነት የሚጠየቁ ከፍተኛ አመራሮችን ጉዳይ በመሸፈን ወንጀለኞችንና ወንጀልን እያበረታታ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 አስታወቁ።


ኮሚቴ ተብሎ የተቋቋመው ጥቆማ የቀረበባቸውን ተጠርጣሪዎች በመለየት ምርመራ መጀመሩን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።


ሆኖም ምርመራው ያተኮረው በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ብቻ መሆኑ ዋናውን የወንጀሉን ባለቤቶች የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል ባይ ናቸው።


በተለይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ በአጠገቡ ያሉትን የሌቦች ስብስብ ሁሉ ላለመንካት ኮሚቴው እያደረገ ያለው መሸፋፈን እንዳስቆጣቸውም ይናገራሉ።


የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ጨምሮ በሌብነት የተዘፈቁና ጥቆማ የቀረበባቸው ቢሆንም ኮሚቴው ትኩረት ያደረገው በትርፍ አበል ላይ ብቻ መሆኑ በራሱ አነጋጋሪ ሆኗል ሲሉ አስቀምጠውታል።



የኮሚቴን ስራ በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውን የገለጹት ነዋሪዎች በክልሉ ጥቆማ የቀረበባቸውና በተጨበጭ የማጣራት ሥራ ተሠርቶ መጠዬቅ ያለባቸው ግለሰቦች መለየታቸውን ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል።


በዚህም እስካሁን የተለዩት አንድ መቶ ሃምሳ ግለሰቦች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ባለፈው ሳምንት ወደ ሳላሳ የሚጠጉ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ይናገራሉ

ከእነዚህ መካከል የሀዋሳ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንደሚገኝበት በመረጃቸው ላይ አስቀምጠዋል።


ነገር ግን ይላሉ ነዋሪዎቹ አሁን የታሰሩትም ሆኑ ስማቸው ተለየ የተባሉት አመራሮችና ሰራተኞች ከላይ ላለው አመራር ድጋፍ የሚሰጡ እንጂ ዋና የሌብነቱ ምንጮች አይደሉም ብለዋል።


ስለዚህ ኮሚቴው እየሰራ ያለው ስራ ግልጽነት የጎደለውና ምናልባትም ከላይኛው አመራር ተጽእኖ ያልተላቀቀ በመሆኑ ምንም አይነት ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማይጠብቁም ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page