top of page

ነሐሴ 18/2015 የብአዴን አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን የኢትዮ ገለጹ።


በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃንና አካባቢው መረጃ በመስጠትና መንገድ በመምራት ጭምር ህዝባቸውን እያስጨረሱ ላሉ የብአዴን አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


በማስጠንቀቂያው ላይ በዋናነት በዚህ ክህደት ውስጥ መሪ ተዋናይ የሆኑ አመራሮች ስም ዝርዝርና የሚገኙበት አድራሻ ጭምር ይፋ መሆኑን ነው ምንጮቹ ያመለከቱት።


እነዚህ ስማቸው በዝርዝር የተቀመጠው ሆድ አደር አመራሮች ለገዳዩ ቡድን መረጃ በመስጠት ጭምር እየፈጸሙ ያሉትን ክህደት በአስቸኳይ እንዲያቆሙም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተላለፋቸውም ይናገራሉ።


ይሄን ሳያደርጉ ቢቀሩ ግን ለሚጠብቃቸው ቅጣት ገሌነት የገቡለት ገዳይ ቡድንም እንደማያድናቸው በግልጽ ተቀምጦላቸዋል ይላሉ።


ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን በማስገደል ግንባር ቀደም የሆአው ሻለቃ ባሻ አስፋው ጥላነህ የሚባለው ግለሰብ ሲሆን በኢሃዴግ ጊዜ የመረጃ ሰራተኛ የነበረውና አሁንም ለገዳዩ ቡድን እየሰራ ያለው አዲስ የተባለው ግለሰብ ሌላው መሆኑን ያስቀምጣሉ።


በለጠ ገድለ አማኑኤል የተባለው ግለሰብም ሌላኛው የአማራ ህዝብ ጠላት ሲሆን የስራ ድርሻውም የአካባቢው ሚሊሻ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።


ሰለሞን የተባለው ግለሰብም የደብረብርሃን ከተማ መረጃ ሰላም እና ደህንነት ሰራተኛ ሲሆን ለአማራ ህዝብ ደግሞ ከባድ አደጋን የደቀነ ሰው መሆኑን አስቀምጠዋል።


በሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ወረዳ መንዝ ደብረብርሃን ላይ ቁጭ ብለው መረጃ በመስጠት ንጹሃንን እያስጨረሱ ያሉት የወረዳው አስተዳዳሪ ሃይሌ እንግዳ፣ምክትል አስተዳዳሪው አለሙ ሃይሌ ፣የሰላምና ደህንነት ሃላፊው እንግዳሰው በለጠ፣የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አጅቤ ዘለቀና የወረዳው ብልጽግና ሃላፊ እሴተ ወልደሩፋዔል መሆናቸውንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

ነሃሴ 18/2015 በሰሜን ሸዋ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ /መኮይ/ ገና በጠዋቱ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። ገና ሳይነጋ ንጹሃንን ሊፈጅ ወደ በአንጾኪያ...

ነሐሴ 18/2015 የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ገለጹ።

በደቡብ ክልል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ክልል ውስጥ ያሉው የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ። አዲስ ተቋቋመ በተባለውና ከፍተኛ ቁጥር...

ነሐሴ 18/2015 የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች በአዲስ መልክ ተደራጅተው መነሳታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

የአማራ ክልልን ወደሌላ ብጥብጥና ቀጠና ለማምራት የተነሱ የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች በአዲስ መልክ ተደራጅተው መነሳታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ። እነዚህ ቡድኖች የብአዴንን ሽንፈት አምነው መቀበል...

Comments


bottom of page