ነሐሴ 18/2015 የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች በአዲስ መልክ ተደራጅተው መነሳታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።
- Ethio 360 Media 2
- Aug 24, 2023
- 1 min read
የአማራ ክልልን ወደሌላ ብጥብጥና ቀጠና ለማምራት የተነሱ የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች በአዲስ መልክ ተደራጅተው መነሳታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
እነዚህ ቡድኖች የብአዴንን ሽንፈት አምነው መቀበል ያልቻሉና አሁንም በአማራ ንጹሃን ዜጎች ደም ላይ የሚነግዱ የከሃዲው የብአዴን ስብስብ ናቸው ይላሉ።
ይሄንን ብጥብጥ በዋናነት የሚመሩት ሰዎች እነማን ናቸው የሚለው የተለየ ሲሆን በምንም ውስጥ የሌሉ ምልምሎችን ከተማዋ ላይ ማሰማራቱን ይናገራሉ።
ኮሚሽነር አትንኩትና የከተማ ከንቲባ በጋራ በመሆን የጀመሩት የአማራ ህዝብን ዳግም ለሞት ሊዳርጉት ከተዘጋጁት ዋነኞቹ ናቸው ይላሉ ሲሉም ይገልጿቸዋል።
ይሄንን ፍጅት ለመሳካት ደግሞ አካባቢውን በማያውቅ የሚሊሻ ሃይል አስወርረውታል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።