(ኢትዮ 360-ሚያዚያ 25/2015) በሰሜን ሸዋ ሸዋ ሮቢትና አካባቢው የኦህዴዱ መከላከያ ሰራዊት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጦርነት መክፈቱን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ትላንት ከአካባቢው ወደ ደብረሲና ሸሽቶ የነበረው ሃይል ዛሬ ላይ ሃይሉን አጠናክሮ መምጣቱን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ ኬላውን ዘግቶ የነበረ ቢሆንም ያንን አልፎ የገባው ገዳዩ ቡድን ከጥቃቱ ሌላ ህብረተሰቡንም እያፈነ ነው ሲሉም ለኢትዮ 360 ተናግረዋል፡።
አሁን በንጹሃን ዜጎች ላይ የተከፈተው ጦርነት ሌላ ነገር ሳይሆን ክህደት ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ ።
ከራሳ ሃይል በመጨመር ህዝብን እየጨረሰ ያለው ይሄ ቡድን ራሱ በአካባቢው በጫረው ጠብ ነው ከፋኖ ህዝባዊ ሃይል ጋር ጦርነት ውስጥ የገባው ይላሉ።
ገዳዩ ቡድን አሁን ላይ ጦርነት እያካሄደ ያለው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ነዋሪው ወዴትም እንዳይንቀሳቀስ አድርጎ በማፈን ጭምር ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ይሄንን ገዳይ ቡድን የሚታገለው የፋኖ ህዝባዊ ሃይሉን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ እምቢተኝነቱን ማሳየት አለበት ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ትላንት እነሱ አደባባይ በመውጣት ጭምር ይሄንን ሃይል ለመጋፈጥ በሞከሩት ልክ ሁሉም መታገል አለበትም ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።