በሃድያ ዞን የ3 ወር ደሞዝ ያልተከፈላቸው የመንግስት ሰራተኞች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
የሶስት ወረዳና የአንድ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የሶስት ወር ደሞዛቸውን በተደጋጋሚ ቢጠብቁም የሚሰጣቸው ግን ማግኘት እንዳልቻሉ ይናገራሉ። በተለይ ለበአል ገንዘቡ ይገባላችኋል ቢባልም ያም ግን ተግባራዊ መሆን አልቻለም ይላሉ።
በአካባቢው የመልካም አስተዳደር ችግር ቢኖርም በአሁን ሰአት ግን ዋናው ጉዳይ የደሞዝ ጉዳይ ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ። በምስራቅ ባደዎች፣በምዕራብ ማዶዎች፣በስራሮ ባደዎችና በሾኔ ከተማ አስተዳደር ላለፉት ሶስት ወራት ደሞዝ ያልተከፈለው ማህብረሰብ አደባባይ ለመውጣት ተገዷል ብለዋል። የመንግስት ሰራተኛው ጥያቄውን ሲያቀርብ ደግሞ ዋና መተላለፊያ የሚባሉ መንገዶችን የሚያገናኘውን ዋና መስመሮችን በመዝጋት ጭምር መሆኑንም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ዛሬም ተቃውሞው ሌሎች መንገዶችን በመዝጋት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 የገለጹት። ሾኔ ከምትባለው ከተማ ጀምሮ ዋና የሚባሉ መንገዶችን ሁሉ በማካተት የመንግስት ሰራተኛው ተቃውሞውን ቀጥሏል ብለዋል። የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል በሸዋና አካባቢው አዲስ ዘመቻ ለመክፈት ሲዘጋጅ ጎንደርና አካባቢውን ደግሞ በከባድ መሳሪያ አስከብቧል።