መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመስቀል በአል በመከበር ላይ ነው።
- Ethio 360 Media 2
- Sep 28, 2023
- 1 min read
ሃገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ድባቡን ያደበዘዘው ቢሆንም የእምነቱ ተከታዮች ግን ባላቸው ሁሉ ወገኖቻቸውን በመርዳት ጭምር በአሉን በማክበር ላይ መሆናቸውን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የገልጹት።
ትላንት የተከበረው የመስቀል ደመራ በአል የእምነቱ ተከታዮች በካብድ ሃዘን ውስጥ ሆነው ማክበራቸውንም ከነበረው ድባብ መረዳት ይቻል እንደነበር ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ሌላው ግን ይላሉ ምንጮቹ በአሉ ከሌላ ጊዜ በተለየ ደብራት እየተጠሩ ሳይሆን በብሔር እየተለየ መዘምራን ወደ መስቀል አደባባይ እንዲያልፉ መደረጉን ላይ ሃይማኖታዊውንና ታሪካዊውን የመስቀል በአል የሚያከብር ሳይሆን የብሔር ብሔረሰቦች በአል የሚከበር ይመስል ነበር ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።
የቤተክርስቲያኗ አባቶች ለምን በዛ ደረጃ የቤተክርስቲያኗን ክብር የሚነካ ነገር ለማድረግ ደፈሩ የሚለው የሁሉም ጥያቄ ሆኖ ማለፉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።