top of page

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።


በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።


ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።


ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ላይ በተመሳሳይ ሲፈጸም እንደነበርም አስታውሰዋል።


አሁን ላይ አፈና እየካተሄደባቸው ያሉ አየርመንገዱ ሰራተኞች ደግሞ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።


ከታፈኑት መካከል የደህንነት አገልግሎት፣የአውሮፕላን ጥገና የሒሳብ ክፍል ሰራተኞችና ሌሎች ባለሙያዎች መሆናቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ለማሳያነት እነዚህ ክፍሎች ይጥሩ እንጂ አፈናው እየተካሄደ ያለው ግን በሁሉ የአየር መንገዱ ክፍል ውስጥ መሆኑን ይናገራሉ።


ለዚህ ደግሞ ዋናው አሳፋኙ እና አሳሳሪው እንግልት እንዲፈፀም የሚያደርገው ባለጊዜው በአየርመንገዱ ውስጥ የCorporate Security Service director ሀላፊ ተደርጎ የተሾመ ሒርፓ አዱኛ መሆኑን በግልጽ አስቀምጠዋል።


ባለፉት ቀናት ብቻ የደህንነት ምርመራ ባልደረቦች የሆኑት አበራ ተገኔና የኔሰው አረጋ እንዲሁም የደህንነት ምርመራ ክፍል በሃላፊነት የሚሰሩት አለበል ሁነኛውና አቤል አላምረው መሆናቸውን ያነሳሉ።


የደህንነት መርመራ ስራ አስኪያጅ ፋሲካ ተስፋውና የደህንነት ምርመራ የቡድን መሪ መስፍን ዮሐንስና ሌሎች ከታፈኑት መካከል መሆናቸውንም ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

መስከረም 17/2016 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እነጎበዜ ሲሳይንና ሌሎቹን የሚሰልል ሰው መመደቡን የኢትዮ 360 ምንጮች ተገለጹ።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት 6ኛ የታሰሩት እነ ጎበዚ ሲሳይ ጋ ወርቁ ደምሴ የሚባል በጣም አደገኛና በማረሚያ ቤቱ የቆየ እስረኛ ወደ እነሱ ክፍል እንዲዛወር መደረጉን አስታውቀዋል። ይሄ ግለሰብ ከዚህ በፊት በርካታ ሰዎችን...

bottom of page