መስከረም 17/2016 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እነጎበዜ ሲሳይንና ሌሎቹን የሚሰልል ሰው መመደቡን የኢትዮ 360 ምንጮች ተገለጹ።
- Ethio 360 Media 2
- Sep 28, 2023
- 1 min read
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት 6ኛ የታሰሩት እነ ጎበዚ ሲሳይ ጋ ወርቁ ደምሴ የሚባል በጣም አደገኛና በማረሚያ ቤቱ የቆየ እስረኛ ወደ እነሱ ክፍል እንዲዛወር መደረጉን አስታውቀዋል።
ይሄ ግለሰብ ከዚህ በፊት በርካታ ሰዎችን ያስጨረሰ መሆኑና በፊትም የህወሃት ሰው ሆኖ በርካቶችን ያስመታ መሆኑን ይናገራሉ።
አሁን ደግሞ ባለጊዜው ነኝ በሚል ካርታ ቀይሮ በመምጣት ወደ ጎበዜ ሲሳይ መወሰዱን ገልጸዋል።
ከአንድ ቀን በፊት ምሽት ተጠብቆ ወደ ጎበዜ ክፍል የሄደው ይሄው አደገኛ እስረኛ በዞን 1 ማሰሪያ ውስጥ የቆየ መሆኑንም ጠቁመዋል።