መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ
- Ethio 360 Media 2
- Sep 28, 2023
- 1 min read
መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል።
አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት።
አቃስታ ላይ ወሳኝ የምትባለውን ገነቴን ሙሉ በሙሉ ነጻ ያደረገው ህዝባዊ ሃይሉ ወይና አምባንም ነጻ ማውጣቱን ነው የሚናገሩት።
ሚዳ መርሃቤቴ መራኛ ላይ ህዝባዊ ሃይሉ በወሰደው ርምጃ ሙትና ቁስለኛ የሆነውን ገዳይ ቡድን ጭነው መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
ባለፈው እሁድ መራኛ ላይ ነዋሪውን ስብሰባ ጠርቶ 40 ሰው ብቻ የተገኘለት የገዳዩ ቡድን ስብስብ አስተባባሪ ኮለኔል የማንንም መንደር ወጠጤን በአደባባይ እንሰቅለዋለን በሚል ዛቻ እያሰማ መሆኑንም ተናግረዋል።
ይሄ ዛቻ ዝም ብሎ የሚታይ እንዳልሆነና ይሄንን ተከትሎ ትላንት በንጹሃን መኖሪያ ላይ ሲወስድ የነበረው ርምጃ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአካባቢው አሁንም እያስቸገሩ ያሉ ሆድ አደር ስብስቦችን በመረጃና በስም መለየት ተችሏል፣አላርፍ ካሉም ወደ ርምጃ ለመግባት እንደሚገደዱም አስጠንቅቀዋል።
በአካባቢው ያሉና በህበረተሰቡ ተቀባይነት ያላቸው አመራሮችን ወደ መግደልና ህዝባዊ ሃይሉ ገደለ ለማለት የሚሰሩ ስራዎች መኖራቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።