top of page

ሐምሌ 12/2015 በቅርስነት ተመዝግቦ የሚገኘው የራስ ከበደ መንገሻ ቤት በኦህዴዱ ስርአት ሊፈርስ ነው !


በቅርስነት ተመዝግቦ የሚገኘው የራስ ከበደ መንገሻ ቤት በኦህዴዱ ስርአት ሊፈርስ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1890 ዓም የተገነባውና አሁን ላይ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ለቢሮነት ይገለገልበት የነበረው ቤት ዛሬ ላይ ከፌደራሉ ቤቶች ቅርንጫፍ ሶስት ጽህፈት ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ቅርሱን መጠበቅ መብት እንደሌላቸው በመግለጽ ቤቱን በላያቸው ላይ እንዳሸጉባቸው ምንጮቹ ተናግረዋል።


ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅርሶቹን በማፍረስ የከተማውን ታሪክ ለመቀየር እየለፋ ያለው ይሄው የህገወጦች ስብስብ ቦታውን አስቀድሞ ከባለጊዜው ባለሃብቶች ጋር እንደተደራደረበትም አመልክተዋል።


በቦሌ መንገድ ፒኮክ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኘው ይሄው ቅርስ አስቀድሞም ቢሆን አያናቸውን ጥለውበት እንደቆዩና የቅርስ ባላደራ ሰዎች በመኖራቸው ብቻ እስካሁን መቆየቱን ይናገራሉ።


አሁንም የቅርስ ጥበቃ ሰዎች ፍርድ ቤት ድረስ ለመሔድና ቅርሱን ለማስጠበቅ ጥረት ቢያደርጉም መብት የላችሁም የሚል መስል እንደተሰጣቸውንም ገልጸዋል።


ከዚህም ተነስቶ አሁን ላይ ቤቶቹን ያሸገው አካል ምናልባትም በአንዱ ቀን ቅርሱን አፈራርሶት እንደሚያድርም ምንጮቹ በእርግጠኝነት ይናገራሉ።


ያ ከመሆኑና ቅርሱ ወደ አመድነት ከመቀየሩ በፊት ሁሉም ኢትዮጵያዊም ሆነ የሚመለከተው አካል ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ጭምር ቅርሱን እንዲታደግ አስቸኳይ ጥሪ እየቀረበ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


ይህ ቅርስ የራስ ከበደ መንገሻ አይቲከም መኖሪያ ቤት የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓት የቅርስ ባላደራ ጽሕፈት ቤት እየተገለገለበት ያለ ሲሆን የሚገኘውም ቦሌ መንገድፒኮክ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ሲሆን በኪራይ ቤቶች ስም ቅርስ ለማውደም የሚያደርጉት ጉዞ አንዱ አካል ነው ቅርስ ባላደራ ደውላችሁ ማረጋገጥ ይቻላል።



ከቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት የሚገኘው በዳግማዊ ምኒሊክ ዘመን በ1890 ዓም የተገነባው የራስ ከበደ መንገሻ ቤት የነበረውና በቅርስነት ተመዘግቦ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ለቢሮነት የሚገለገልበትን እንዲለቁ መደረጉን ገልጸዋል። Ethiopian Heritage Trust - #Ethiopia ‹‹ለቅርስ ባለአደራ ድምፅ በመሆን እንታደገው!!››



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page