መንግስት የሚባለው አካል "ጽንፈኛ" በሚል እሳቤ አማራነታቸውን መሰረት አድርጎ ያሰራቸውን የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ ባለሀብቶች እና ሌሎች ግለሰቦችን በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲል እናት ፓርቲ አሳሰበ።
መንግስት እየተከተለ የሚገኘው ፍኖትም አክሳሪ የፖለቲካ አካሄድ ነው ሲል ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫው ላይ ተችቶታል።
መንግስት አይነኬ የሆነውን ማህበረ-ባህላዊ እሴት በመጣስ በመምህር ኃይለማርያም ዘውዱ ላይ እያደረሰ ያለውን እንግልት እና እስር በአስቸኳይ አቁሞ በክብር ወደ ነበሩበት የሥራ ገበታቸው እንዲመልሳቸው ሲልም ፓርቲው በመግለጫው አሳስቧል።
የእናት ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አሰፋ አዳነ ፍርድ ቤት የታሰሩበትን ትሾ በዋስ እንዲፈቱ ብይን ተሰቷል፣ስለዚህ "በዋስ ይፈታ ብይን" ተከብሮ ከእስር እንዲለቀቁ እንዲያደርግም ጥያቄውን አቅርቧል።
መንግሥት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ እና አጎራባች ቀበሌዎች እንዲሁም በእኖር ወረዳ በሚገኙ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች እና በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ያለውን መልካም ትስስር ለማጠልሸት እየሰሩ የሚገኙ አካላትን በመለየት በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ ሲልም እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫው ጥሪውን አቅርቧል።